am_tn/ezk/23/11.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ የኢየሩሳሌም እና ሰማርያ ከተሞችን እንደ ሁለት አመንዝሮች አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ ይህ ዘይቤ እስከ ሕዝቅኤል 23፡34 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኦሖሊባ

ይህ የሴት ስም ሲሆን ትርጉሙ "የእኔ ድንኳን በእርሷ ነው" ማለት ነው፡፡ ይህ ስም በሕዝቅኤል 23፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

መርከስ/ንጹህ አለመሆን

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ነገር ንጹህ አድርጎ የማይቆጥረው ወይም የረከሰ ሰው በአካል እንደቆሸሸ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ ይህ ስም በሕዝቅኤል 23፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ለሁለቱም እህትማማቾች ተመሳሳይ/አንድ ነበር

ይህ የሚያመለክተው ሁለቱም እንዴት ራሳቸውን እንዳረከሱ ነው፡፡ "ሁለቱም እህትማማቾች በምንዝርና ተግባራቸው ረክሰዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)