am_tn/ezk/22/30.md

2.3 KiB

ቅጥርን የሚሠራ ከእነርሱ አንድ ሰው

ይህ የሚናገረው ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ለመከላከል ቅጥር የሚሠራ ሰውን ይመስል ስለ ሕዝቡ ለመጸለይና ወደ ንስሐ ሊመራቸው ኃላፊነት ስለሚወስድ አንድ ሰው። አ.ት፡ “ከመካከላቸው ልክ ቅጥርን እንደሚሠራ የሚያደርግን ሰው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በፈረሰው በኩል በፊቴ የሚቆም

“በፈረሰው” የሚያመለክተው በቅጥሩ መካከል ያለውን ክፍተት ነው። ይህ የሚናገረው ከተማይቱን ለመከላከል በፈረሰው በኩል እንደሚቆም ተዋጊ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ስለሚከላከል ሰው ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንዳላጠፋት ስለምድሪቱ

እዚህ ጋ፣ “ምድር” በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “እንዳላጠፋቸው ስለ ሕዝቡ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መዓቴን አፈስባቸዋለሁ

መዓቱ በእነርሱ ላይ የሚያፈሰው ፈሳሽ የሆነ ይመስል ይህ የሚናገረው እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚቀጣበት ሁኔታ ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መዓት

ፍትሕ በማጣት የሚሰቃይ ሰው ቁጣ

በመዓቴ እሳት እጨርሳቸዋለሁ

ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ከእሳት ጋር በማነጻጸር ይናገራል። እዚህ ጋ፣ ሕዝቡን ማጥፋት እነርሱን እንደ “መጨረስ” ተደርጎ ተመልክቷል። አ.ት፡ “እንደሚንበለበል እሳት ብርቱ በሆነው ቁጣዬ አጠፋቸዋለሁ” ወይም “በቁጣዬ አጠፋቸዋለሁ”

መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ አመልሳለሁ

አንድን ነገር በሰው ራስ ላይ ማስቀመጥ ሸክም እንዲሸከሙ ወይም ስለ ጉዳዩ ኃላፊነት እንዲወስዱ ማድረግን ያመለክታል። አ.ት፡ “ስላደረጉት ነገር ኃላፊነት እንዲወስዱ አደርጋቸዋለሁ”