am_tn/ezk/22/26.md

2.5 KiB

እርሷ

ይህ ተውላጠ ስም ኢየሩሳሌምን ያመለክታል።

በሕጌ ላይ ያምፃሉ

“ሕጌን አይታዘዙም”

እርኩሱ እና ንጹሑ

ይህ እርኩስና ንጹሕ የሆኑ ነገሮችን ያመለክታል። እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት የለውም ወይም እረክሷል የሚለው አንድ ነገር፣ እርሱ በአካሉም የረከሰ ያህል ተቆጥሮ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “እርኩስ የሆኑና ንጹሕ የሆኑ ነገሮች” (ስማዊ ቅጽል እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዐይኖቻቸውን ከሰንበቶቼ ይደብቃሉ

ሕዝቡ ዐይኖቻቸውን ከሰንበት ይደብቁ ይመስል ይህ የሚናገረው ሰንበትን ቸል ስለማለታቸውና ስላለመጠበቃቸው ነው። አ.ት፡ “ሰንበቶቼን ቸል ይላሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለዚህ በመካከላቸው ተንቄአለሁ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በመካከላቸው ይንቁኛል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

መሳፍንቶቿ በውስጧ ልክ ንጥቂያቸውን እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው

ይህ የእስራኤልን መሳፍንት ንጥቂያዎቻቸውን ከሚያጠቁና ከሚገድሉ ተኩላዎች ጋር ያነጻጽራቸዋል።

ደም ያፈሳሉ፣ ሕይወትንም ያጠፋሉ

በመሠረቱ የእነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉም አንድ ሲሆን መሳፍንቱ በሚፈጽሟቸው ግፎች ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ሰዎችን ይገድላሉ”

ነቢያቶቿ በኖራ ቀብተዋቸዋል

ይህ የሚናገረው ነቢያቱ በኖራ እንደሚቀቡት አንዳች ነገር እነዚህን ኃጢአቶች ለመደበቅ መሞከራቸውን ነው። አ.ት፡ “ነገሩ ነቢያቶቿ ኃጢአታቸውን በኖራ የቀቡት ያህል ነው” ወይም “ነቢያቶቻቸው እነዚህን ክፉ ነገሮች ለመደበቅ ይሞክራሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ኖራ

ይህ ከነጭ ቀለም ጋር ተመሳሳይ ሲሆን አንዳንድ ነገሮችን ነጭ ለማድረግ የሚቀባ ውሁድ ነው።

ሐሰትን ተንብየውላቸዋል

x