am_tn/ezk/22/23.md

2.8 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

አንቺ ያላነጹሽ ምድር ነሽ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። እዚህ ጋ፣ “ምድር” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እስራኤልንና በዚያ የሚኖሩትን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ንጹሕ ያልሆነው ምድርና ሕዝብ አንቺ ነሽ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ያላነጹሽ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት እንደሌለው ወይም እንደ ረከሰ የሚቆጥረው ሰው ያ ሰው በአካሉም እንደ ረከሰ ተቆጥሮ ተነግሮለታል።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በቁጣ ቀን ምንም ዝናብ የለም

ዝናብ የእግዚአብሔር በረከት ምሳሌ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “በቁጣ ቀን ምንም በረከት የለም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በመካከሏ የነቢያቶቿ ሤራ አለ

“እርሷ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እስራኤልን ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል ያሉ ነቢያት ሤራዎችን አሲረዋል”

ሤራ

ሕገ ወጥ ወይም የሚጎዳ ነገር ለማድረግ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች በምስጢር የሚደረግ ዕቅድ

ልክ እያገሳ ንጥቂያውን እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ ሕይወትን ያጠፋሉ፣ የከበረውን ሀብትም ይወስዳሉ

ይህ የእስራኤልን ነቢያት ንጥቂያዎቻቸውን ከሚያጠቁና ከሚገድሉ አናብስት ጋር ተነጻጽረዋል። አ.ት፡ “ያደኑትን እንደሚያጠቁና እንደሚገድሉ የሚያገሱ አንበሶች ሰዎችን ይገድላሉ። የሰዎችን የከበሩ ሀብቶች ይወስዳሉ”

በውስጣ ብዙ መበለቶች እንዲኖሩ ያደርጋሉ

“እርሷ” የሚለው ቃል እስራኤልን ያመለክታል። ያገቡትን ወንዶች በመግደል “ብዙ መበለቶች እንዲኖሩ ያደርጋሉ”። አ.ት፡ “ባሎቻቸውን በመግደል ብዙ ሴቶችን መበለቶች ያደርጓቸዋል”