am_tn/ezk/22/17.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት አለው

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያን አላቸው” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን አላቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጉድፍ ሆኑብኝ

ጉድፍ፣ ብር ወይም ወርቅ በምድጃ ላይ ከነጠረ በኋላ የሚቀር ብካይ ነው። እዚህ ጋ ሕዝቡ እንደ ጉድፍ እንደማይጠቅሙት እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ለእኔ እንደ ጉድፍ የማይጠቅሙኝ ሆነዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሁሉም ከነሐስና ከቆርቆሮ እንደሚተርፍ … በምድጃችሁ እንዳለ የብር ጉድፍ ናቸው

ሕዝቡ ጉድፍ የሆኑ ይመስል ምንም የማይጠቅሙት እንደሆኑበት እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጣላል። አ.ት፡ “ሁሉም ምድጃ ውስጥ ብርን ካቀለጥከው በኋላ ከነሐስና ከቆርቆሮ፣ ከብረትና ከእርሳስ እንደሚቀር ትራፊ የማይጠቅሙ ናቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነሆ

“ተመልከቱ” ወይም “ስሙ” ወይም “የምነግራችሁን ልብ በሉ”