am_tn/ezk/22/13.md

4.1 KiB

እጄን አማታሁ

“በአንቺ ላይ ቡጢዬን ወዝውዣለሁ” ወይም “በአንቺ ላይ እጆቼን አጨብጭቤአለሁ”። ይህ ቁጣንና ተቃውሞን የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “በአንቺ ላይ ቁጣዬንና ተቃውሞዬን አሳይቻለሁ” (ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)

በመካከልሽ የተደረገውን ደም ማፍሰስ

“በውስጥሽ ያሉ ሰዎች የፈጸሙት ግድያ”

እኔ ራሴ ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ጊዜ በልበ ሙሉነት ትቆሚያለሽ? በእነዚያ ቀናት እጆችሽስ ይጠነክራሉ?

እግዚአብሔር በሚቀጣቸው ጊዜ ምን ያህል እንደሚጎዱ አጽንዖት ለመስጠት ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠቀማል። ይህ ጥያቄ ምናልባት እንደ ንግግር ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ራሴ ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ቀን በልበ ሙሉነት አትቆሚም፣ እጆችሽም አይጠነክሩልሽም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በልበ ሙሉነት ትቆሚያለሽ?

እዚህ ጋ ስሜቱና ፈቃዱ ላይ አጽንዖት ለመስጠት ሙሉው ሰው “ልብ” በሚል ቃል ተመላክቷል። እዚህ ጋ የ “መቆም” አሳብ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን በድፍረት ማለት ነው። አ.ት፡ “ትቆሚያለሽ?” ወይም “ደፋር ትሆኛለሽ?” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

እጆችሽስ ይጠነክራሉ?

እዚህ ጋ ሙሉው ሰው በ “እጆቹ” ተመላክቷል። አ.ት፡ “ብርቱ ትሆኛለሽ?” (See: Synecdoche)

ስለዚህ በሀገራት መካከል እበትንሻለሁ፣ በምድር ሁሉ ላይ እበታትንሻለሁ

የእነዚህ ሁለት ሐረጎች መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 12፡15 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ስለዚህ እርስ በእርሳቸው እንዲለያዩና በተለያየ ሀገር እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ”

ማጽዳት

አንድ የማይፈለግን ነገር ማስወገድ

እርኩስ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት የለውም ወይም እረክሷል የሚለው አንድ ሰው፣ እርሱ በአካሉም የረከሰ ያህል ተቆጥሮ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለዚህ፣ በሀገሮች ዐይን ፊት እርኩስ ትሆኛለሽ

እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚያመለክተው በእነዚያ አካባቢዎች የሚኖሩትን ሰዎች ነው። “ዐይን” ማየትን፣ ማየትም አሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል። አ.ት፡ “ስለዚህ፣ ሀገሮች እርኩስ እንደሆንሽ ይቆጥራሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሀገሮቹ

እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚያመለክተው በእነዚያ አካባቢዎች የሚኖሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በሌሎች ሀገሮች የሚኖሩ ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ

እግዚአብሔር ሰዎች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ ብሎ በሚናገርበት ጊዜ እርሱ ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሰዎች ያውቃሉ ማለቱ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 6፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እውነተኛው አምላክ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይረዳሉ” ወይም “ፍጹም ኃይልና ሥልጣን ያለኝ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይገነዘባሉ”