am_tn/ezk/22/10.md

3.9 KiB

በውስጥሽ

በዚህ ሐረግ በየትኛውም አገባብ፣ ጸሐፊው የኢየሩሳሌምን ሰዎች ከተማውን ራሱን እንደ ሆኑ፣ የኢየሩሳሌም ከተማንም ሴት እንደሆነች አድርጎ ያመለክታል። አ.ት፡ “በዚህች ከተማ ውስጥ” ወይም “በእናንተ በኢየሩሳሌም ሰዎች መካከል” (Apostrophe፣ ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወንዶች የአባቶቻቸውን ራቁትነት ገልጠዋል

ይህ ማለት ወንዱ ልጅ ከአባቱ ሚስት ጋር ይተኛል። አ.ት፡ “ከአባቶቻቸው ሚስቶች ጋር የሚተኙ ወንዶች አሉ”

በወር አበባቸው ወቅት የረከሱትን ሴቶች አስገድደዋል … ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር አስጸያፊ ተግባር ፈጽመዋል … የልጆቻቸውን ሚስቶች በሚያሳፍር ሁኔታ አርክሰዋል … የገዛ እህቶቻቸውን አስነውረዋል

ወንዶቹ ሊያደርጉት የማይገባቸውን ከሴቶች ጋር በመተኛታቸው፣ ተግባራቸው ምን ያህል ኃጢአትን የተሞላ እንደሆነ እነዚህ ሁሉ መግለጫ መንገዶች ናቸው። አ.ት፡ “በወር አበባቸው ወቅት የረከሱትን ሴቶች ደፍረዋል … ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር በመተኛት አስጸያፊ ተግባር ፈጽመዋል … ከእነርሱ ጋር በመተኛታቸው የልጆቻቸውን ሚስቶች በሚያሳፍር ሁኔታ አርክሰዋቸዋል … የገዛ እህቶቻቸውን ደፍረዋል”

እርኩስ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት የለውም ወይም እረክሷል የሚለው አንድ ሰው፣ እርሱ በአካሉም የረከሰ ያህል ተቆጥሮ ተነግሮለታል። ሴቶች በወር አበባቸው ወቅት እርኩስ እንደሆኑ ይቆጠሩ ነበር። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ደም ለማፍሰስ

ይህ ደምን ማፍሰስ የሚናገረው ሰዎችን ስለ መግደል ነው። አ.ት፡ “ሰዎችን ለመግደል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ወለድ

ይህ ቃል ተበዳሪው ለተበደረው ገንዘብ የሚከፍለውን ገንዘብ ያመለክታል። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ አዳዲስ ትርጉሞች በዚህ ምንባብ ያለውን “የትኛውም ወለድ” የሚለውን “እጅግ የበዛ ወለድ” ብለው ይተረጉሙታል።

ባልንጀሮችሽን በመጨቆን ጎድተሻቸዋል

ይህ ማለት እጅግ የበዛ ወለድ በማስከፈል ባልንጀሮቻቸውን ጨቁነዋል። አ.ት፡ “ባልንጀሮቻችሁን በመጨቆን ድኻ አ”ድርጋችኋቸዋል” ወይም “እጅግ ብዙ ወለድ በማስከፈል ባልንጀሮቻችሁ እንዲደኸዩ አድርጋችኋል”

እረስተሽኛል

እግዚአብሔርን ለመታዘዝ እምቢ ማለት የእርሱን መኖር እንደ መርሳት ማለት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)