am_tn/ezk/22/06.md

1.6 KiB

እነሆ

“ተመልከቺ” ወይም “ስሚ” ወይም “የምነግርሽን ልብ በይ”

እያንዳንዱ በራሱ ኃይል መጥቷል

“እያንዳንዳቸው ወደ አንቺ ለመምጣት ሥልጣናቸውን ተጠቅመዋል”

ወደ አንቺ መጥተዋል … በመካከልሽ

“ወደ ከተማሽ መጥተዋል … በከተማሽ ውስጥ”። “አንቺ” እና “የአንቺ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ኢየሩሳሌምን ነው።

ደም ለማፍሰስ

ይህ ደምን ማፍሰስ የሚናገረው ሰዎችን ስለ መግደል ነው። አ.ት፡ “ሰዎችን ለመግደል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በአንቺ ውስጥ ያሉትን አባቶችና እናቶች አዋርደዋል

“የኢየሩሳሌም ሰዎች አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን አዋርደዋል”። “እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢየሩሳሌምን ሰዎች ነው።

ጭቆናን ፈጽመዋል

“ጨቁነዋል”

በተራሮቹ ላይ ይበላሉ

እዚህ ጋ “ተራሮቹ” የሚያመለክቱት በተራሮቹ ላይ ለጣዖታቱ የተለዩትን መሰዊያዎች ነው። ወንዶቻቸው ከሐሰተኞቹ አማልክት በረከትን ለማግኘት ለጣዖታቱ የሚሰዋውን ሥጋ ይበላሉ። አ.ት፡ “ለጣዖታት የተሰዋ ሥጋ ይበላሉ”

በመካከልሽ ክፋትን ይፈጽማሉ

“በመካከልሽ ክፉ ነገሮችን ያደርጋሉ”