am_tn/ezk/22/04.md

2.3 KiB

ባፈሰስሽው ደም

ይህ ሰዎችን መግደል ደምን እንደ ማፍሰስ መሆኑን ይናገራል። አ.ት፡ “ንጹሐን ሰዎችን ስለ ገደልሽ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እርኩስ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት የለውም ወይም እረክሷል የሚለው አንድ ሰው፣ እርሱ በአካሉም የረከሰ ያህል ተቆጥሮ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቀንሽን አቅርበሻል፣ የዘመንሽ መጨረሻም መጥቷል

የቀኖች መቅረብና የዘመን መጨረሻ መምጣት ምስሎች ሁለቱም የአነጋገር ዘይቤዎች የሚወክሉት በሞት ወይም በመደምሰስ መጥፋትን ነው። ኢየሩሳሌም ቀኖቿን አቅርባለች በማለት በሕዝቡ ኃጢአት ምክንያት ኢየሩሳሌም በቶሎ እንደምትጠፋ እግዚአብሔር ያመለክታል። አ.ት፡ “ባደረግሻቸው በእነዚህ ነገሮች ምክንያት ወደ ፍጻሜሽ ቀርበሻል” ወይም “ሕልውናሽ እንዲያበቃ አድርገሻል”

ቀንሽን አቅርበሻል

“መጨረሻሽን አምጥተሻል” ወይም “ሕይወትሽን ጨርሰሻል”

ለሀገሮች ዘለፋ ለምድርም ሁሉ መሳለቂያ አደርግሻለሁ

ስም የሆኑት “ዘለፋ” እና “መሳለቂያ” እንደ ግሥ ይገለጹ ዘንድ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ሀገራት እንዲዘልፉሽ፣ ምድርም ሁሉ እንዲስቁብሽ አደርጋቸዋለሁ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

ዘለፋ

ሰዎች የሚቃወሙት ወይም የሚገስጹት ሰው

መሳለቂያ

ሰዎች የሚያሞኙት ወይም የሚያሾፉበት ሰው

ለምድር ሁሉ

ይህ ጥቅል አስተያየት የሚያመለክተው ለኢየሩሳሌም ቅርበት ያላቸውን ቦታዎችና በእነዚህ ቦታዎች ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “በአቅራቢያ ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)