am_tn/ezk/22/01.md

3.2 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

አሁንም አንተ፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ትፈርዳለህ? በደም ከተማ ላይ ትፈርዳለህ?

ይህ ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እንደ ትዕዛዝ ያገለግላል። አ.ት፡ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ሂድና ፍረድ። ሂድና በደም ከተማ ላይ ፍረድ”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

የደም ከተማ

“ደም” የሚለው ቃል የመግደል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎች ባልንጀሮቻቸውን የሚገድሉባት ከተማ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እርሷ … ራሷ

“እርሷ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው። አብዛኛውን ጊዜ ከተሞች እንደ ሴት ይታሰቡ ነበር። ይህ እስከ ቁጥር 32 ይቀጥላል። (ተባዕት ቃል ሴትን በሚጨምርበት ጊዜ እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት))

በመካከሏ … የምታፈስ ይህቺ ከተማ ናት

እዚህ ጋ “ከተማ” በዚያ የሚኖረውን ሕዝብ ይወክላል። አ.ት፡ “በዚህ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች . . . በመካከሏ ያፈሳሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመካከሏ ደም የሚያፈሱ

“ደም” የሚለው ቃል የመግደል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎች ባልንጀሮቻቸውን የሚገድሉበት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጊዜዋ እንዲመጣ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር እነርሱን የሚያጠፋበትን ጊዜ ነው። አ.ት፡ “የመጥፊያዋ ጊዜ ይመጣ ዘንድ” ወይም “የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣባት ዘንድ”

እርኩስ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሁኔታው ተቀባይነት የለውም ወይም እረክሷል የሚለው አንድ ሰው፣ እርሱ በአካሉም የረከሰ ያህል ተቆጥሮ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)