am_tn/ezk/21/30.md

2.2 KiB

ሰይፉን ወደ ሰገባው መልሰው

“በኋላ ሰይፉ ወደ ሰገባው ውስጥ ተመልሶ ይከተታል”። የእግዚአብሔር ሰይፍ ወደ ሰገባው ተመልሶ ይከተታል በማለት ወታደሮች ኢየሩሳሌምን ከማጥቃት እንደሚመለሱ ይህ ይናገራል። አ.ት፡ “በኋላ ግን የማረድ ጊዜ ስለሚያበቃ ወታደሮች ሰይፎቻቸውን ወደ ሰገባዎቻቸው ይመልሳሉ”

ሰገባ

ማንም በማይጠቀምበት ጊዜ ሰይፉን የሚይዘውና የሚሸፍነው ነገር ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 21፡3 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።

በተፈጠርክበት ቦታ

“መፈጠር” የሚለው ቃል ምናልባት እንደ ግሥ መገለጽ ይኖርበታል። አ.ት፡ “አንተን በፈጠርኩበት ቦታ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

መዓቴን አፈስብሃለሁ

ይህ የእግዚአብሔር መዓት ፈሳሽ ሆኖ ከመያዣ ዕቃው ውስጥ በእነርሱ ላይ የሚያፈሰው በሚመስልበት መልኩ ከመዓቱ የተነሣ እርሱ ባቢሎናውያንን እንደሚቀጣቸው ይናገራል። አ.ት፡ “በአንተ ላይ ከሚሆነው መዓት የተነሣ እቀጣሃለሁ” ወይም “ከቁጣዬ የተነሣ እቀጣሃለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በአንተ ላይ የቁጣዬን እሳት አራግባለሁ

ይህ የእግዚአብሔርን ቁጣ ከሚያቃጥል እሳት ጋር ያወዳድራል። አ.ት፡ “በአንተ ላይ ቁጣዬን እንደሚንቀለቀል እሳት አመጣለሁ” ወይም “በብርቱ ቁጣዬ እቀጣሃለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የጨካኞች እጅ

የሰዎች “እጅ” የሚያመለክተው ቁጥጥራቸውን ነው። አ.ት፡ “የጨካኞች ቁጥጥር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በጥፋት የተካኑ ሰዎች

“ለታላቅ ጥፋት ምክንያት የሚሆኑ ሰዎች”