am_tn/ezk/21/25.md

1.6 KiB

የመቀጣቱ ቀን የደረሰበት

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አሁን የሚቀጣው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአት የመሥሪያ ጊዜው ያበቃለት

“እግዚአብሔር ኃጢአትን በሚያስቀርበት ጊዜ”

ጥምጥም

“የንጉሥ ጥምጥም”። ጥምጥም ነገሥታት የሥልጣናቸው ምልክት እንዲሆን በራሳቸው ላይ የሚለብሱት የተዋበ አነስተኛ ጨርቅ ነው።

ዝቅ ያለው … ከፍ ያለው

ይህ የሚያመለክተው ዝቅ ያለ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ሰዎችና የከበሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “እነዚያ ዝቅ ያሉትን … እነዚያ ከፍ ያሉትን” ወይም “እነዚያ ዝቅ ያለ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን … እነዚያ ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)

አይታደስም

እዚህ ጋ ዘውድ የንጉሡን ኃላፊነት ይወክላል። መሲሑ እስኪመጣ ድረስ ንግሥና አይታደስም። አ.ት፡ “ከዚያ በኋላ ንጉሥ አይኖርም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የተመደበው እርሱ ይመጣል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የመደብኩት ይመጣል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)