am_tn/ezk/21/21.md

2.0 KiB

በመስቀለኛው መንገድ፣ በመጋጠሚያው ላይ

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የሚያመለክቱት ሁለት መንገዶች የሚገናኙበትን ስፍራ ነው። አ.ት፡ “በመስቀለኛ መንገድ ላይ”

ጥቂት ቀስቶችን ይወዘውዛል፣ ከአንዳንድ ጣዖታቱ ምሪት ይጠይቃል፣ ጉበትንም ይመረምራል

እነዚህ የጥንቆላ ልምምዶች ናቸው።

በቀኝ እጁ ላይ የኢየሩሳሌም ምልክት ይኖራል

ይህ ማለት በቀኝ እጁ በኢየሩሳሌም ላይ እንደ ምልክት ያነበበውን፣ ከጥንቆላ ዕቃዎቹ አንዱን ይይዛል። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም ላይ ምልክት የተደረገበት ከጥንቆላ ዕቃዎቹ አንዱ በቀኝ እጁ ላይ ይሆናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቅጥር መደርመሻ

ቅጥር መደርመሻ የተቆረጠ ዛፍ ወይም ጫፉ የሾለ ረጅም ምሶሶ ወይም ጫፉ በብረት የተሸፈነ ነው። ይህ ጫፉን ግንቡ ላይ ለማስደገፍ ብዙ ሰዎች የሚጎትቱት ነበር።

መወጣጫ ለመሥራት

እነዚህ ባቢሎናውያን ወታደሮች በኢየሩሳሌም ግንቦች ላይ መውጣት እንዲችሉ የሠሯቸው ረጃጅም የቆሸሹ መወጣጫዎች ነበሩ።

ማማዎችን መመሸግ

እነዚህ ባቢሎናውያን ወታደሮች የኢየሩሳሌምን ግንብ አሳልፈው ቀስቶችን ለማስወንጨፍ እንዲያስችላቸው በኢየሩሳሌም ዙሪያ የሠሯቸው የእንጨት ማማዎች ነበሩ።

በኢየሩሳሌም ባለ ሰው ዐይን ፊት

ዐይን ማየትን፣ ማየትም አሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ሰዎች አስተሳሰብ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)