am_tn/ezk/21/18.md

1.3 KiB

የእግዚአብሔር ቃል እንደ ገና ወደ እኔ መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል መጣ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 18፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደገና ተናገረኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ

“ሰይፍ” የሚለው ቃል ሰይፍን በመጠቀም ሰዎችን የሚገድሉትን ወታደሮች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የባቢሎን ንጉሥ ወታደሮች” ወይም “የባቢሎናውያን ሰራዊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእነርሱ አንዱ ወደ ከተማ የሚመራቸው የመንገድ ምልክት ይሆናል

ይህ መንገዱ ለሁለት በሚከፈልበት ቦታ ላይ የሚደረግ ምልክት ነው። አ.ት፡ “መንገዱ ወደ ሁለት መንገድነት በሚከፈልበት ቦታ ላይ ምልክት ይቆማል”