am_tn/ezk/21/15.md

3.1 KiB

ልባቸውን ለማቅለጥ

ይህ ልባቸው ይቀልጥ ይመስል ሕዝቡ በጣም እንዲፈሩ እንደሚያደርጋቸው ይናገራል። አ.ት፡ “በሽብር እንዲሞሉ” ወይም “እንዲፈሩ ለማድረግ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሚወድቁት እንዲበዙ

እዚህ ጋ “መውደቅ” የሚያመለክተው በጦርነት የሚሞቱትን ሰዎች ነው። ይህ ማለት እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይገደላል። አ.ት፡ “በመካከላቸው ብዙ ሕዝብ ለመግደል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሰይፉን ለማረድ አስቀምጫለሁ

እዚህ ጋ የእግዚአብሔር ሰይፍ ኢየሩሳሌምን በሰይፍ የሚያጠቁ ሰዎችን ይወክላል። ደግሞም፣ “ማረድ” የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል። አ.ት፡ “ሕዝቡን ለማረድ ሰይፍ የታጠቁ ወታደሮች በሮቻቸው ላይ ሰፍረዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)

በሮቻቸው

“የእነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ነው።

እንደ መብረቅ ተደርጓል

ይህ ሰይፉ በሚገባ መወልወሉንና ብርሃንን እንደ መብረቅ እንደሚያንጸባርቅ ያነጻጽራል። አ.ት፡ “ሰይፌ ተወልውሏል፣ እንደ መብረቅም ያብረቀርቃል” ወይም “እርሱ ተወልውሏል፣ እንደ መብረቅም ብርሃንን ያንጸባርቃል”

ለማረድ ተይዟል

የእግዚአብሔር ሰይፍ ኢየሩሳሌምን በሰይፍ የሚያጠቁ ሰዎችን ይወክላል። አ.ት፡ “ሕዝቡን ለማረድ ተለቋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አንተ ሰይፍ! ወደ ቀኝ ምታ! … ፊትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ ሂድ

እዚህ ጋ ሰይፍ የሚሰማውና በጦርነቱ ጥቅም ላይ ይውል ይመስል እግዚአብሔር የሚናገረው ሕዝቡን ስለሚያጠቁት ስለ እነዚያ ሰዎች ነው። ይህንን ያደረገው በጦርነቱ ጊዜ የሚሆነውን እርሱ እንደሚቆጣጠረው አጽንዖት ለመስጠት ነው። “ፊትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ” የሚለው ሐረግ “ልትሄድ ወደምትፈልግበት ሁሉ” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በሰይፍ ለሚያጠቁት ለእነርሱ እነግራቸዋለሁ፣ ‘ወደ ቀኝ ምቱ! … በየአቅጣጫው አጥቁ’” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሁለቱን እጆቼን አጋጨሁ

“እጆቼን አጨበጨብኩ”። እዚህ ጋ እጆችን ማጨብጨብ ድል የማድረግ ምልክት ነው። አ.ት፡ “በድል አድራጊነት እጆቼን አጨበጨብኩ” (ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)