am_tn/ezk/21/14.md

1.6 KiB

በሁለት እጆችህ አጨብጭብ

ይህ የሀዘኑ ምልክት እንዲሆን እጆቹን ያጨበጭባል ማለት ነው። አ.ት፡ “በጣም ማዘንህን ለማሳየት እጆችህን አጨብጭብ” (ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)

ለሦስተኛ ጊዜ እንኳን

ይህ ብዙ ጊዜ የማለት የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ደጋግመህ” (ደረጃን አመልካች ቁጥሮች እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሊታረድበት ያለ ሰይፍ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎችን ለማረድ የሆነ ሰይፍ ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ብዙዎች ሊታረዱበት ያለ ሰይፍ ነው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎችን ለማረድ የሆነ ሰይፍ ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በየስፍራው የሚወጋቸው

“ከየአቅጣጫው የሚወጋቸው”። ይህንን አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች “ወደ ክፍሎቻቸው የሚገቡ” ብሎ ይተረጉመዋል። ይህ፣ ሰይፉ ስለሚገድላቸው የትም ቢደበቁ ችግር የለውም ማለት ነው።

የሚወጋቸው

“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢየሩሳሌምን ሕዝብና የእስራኤልን ምድር ነው።