am_tn/ezk/21/12.md

1.9 KiB

ያ ሰይፍ በሕዝቤ ላይ መጥቷል! እርሱ በሁሉ ላይ ነው

ሰይፍ በራሱ ገዳይ የሆነ ይመስል ይህ የሚናገረው ሕዝቡን ስለሚገድለው የእግዚአብሔር ሰይፍ ነው። አ.ት፡ “ሕዝቤን ለመግደል ሰይፌን እጠቀምበታለሁ! እርሱን በሁሉም ላይ አመጣዋለሁ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ለሰይፍ ተጥለዋል

ለሰይፍ የተጣሉ በሚመስልበት ሁኔታ ይህ የሚናገረው በሰይፍ ስለ ተገደሉት የእስራኤል መሪዎች ነው። አ.ት፡ “እነርሱ ከሕዝቤ ጋር በሰይፍ ተገድለዋል” ወይም “ሰይፍ ከሕዝቤ ጋር ይገድላቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ታፋህን ምታ

በሕዝቅኤል ባህል አንድ ሰው ታፋውን መምታቱ የሀዘን ምልክት ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች በብዙዎች ባህል የሀዘን ምልክት የሆነውን ደረት መምታትን ይጠቀማሉ። አ.ት፡ “ደረትህን ምታ” (ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)

ይሁንና በትረ መንግሥቱ ዘለቄታ ባይኖረውስ?

ይህ ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው አድማጮች ምን ሊሆን እንደሚችል እንዲያስቡ ለማድረግ ነው። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “በትረ መንግሥቱን ሰይፍ የሚያጠፋው ከሆነ በጣም አስፈሪ ይሆናል” ወይም “ይሁን እንጂ ንጉሡ ሊቋቋመው ካልቻለ በጣም አስፈሪ ይሆናል”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በትረ መንግሥቱ

x