am_tn/ezk/21/10.md

3.7 KiB

ተስሏል፣ … ለድረግ ተወልውሏል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስለዋለሁ… ያደርግ ዘንድ እወለውለዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

መብረቅ እንዲመስል

ይህ ማለት ሰይፉ በቀላሉ ብርሃን ማንጸባረቅና ፈክቶ መታየት የሚችል አንጸባራቂ ይሆናል። አ.ት፡ “እንደ መብረቅ እንዲያብረቀርቅ” ወይም “ብርሃን በእርሱ ላይ እንደ መብረቅ እንዲያንጸባርቅበት” (See: Simile)

በልጄ በትረ መንግሥት መደሰት ይኖርብናል?

ይህ ምላሽ የማይሻ ጥያቄ “ሰይፍ” መቋቋም ስለማይችል የእስራኤል ሕዝብ የንጉሣቸውን ሥልጣን እንደማያከብሩ አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “የይሁዳ ሕዝብ የንጉሣቸውን በትረ መንግሥት አያከብሩም” ወይም “የንጉሣችንን በትረ መንግሥት ኃይል ማክበር የለብንም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ይኖርብናል?

“እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝቅኤልን እና የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (See: Inclusive “We”)

በልጄ በትረ መንግሥት

እዚህ ጋ እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ እንደ ልጁ አድርጎ ያመለክታል። የንጉሡ በትረ መንግሥት ንጉሣዊ አገዛዙን ይወክላል። እዚህ ጋ “እንዲህ ያለው በትር ሁሉ” የሚሉት ቃላት በትረ መንግሥትን ስለሚያመለክቱ የንጉሡን በትረ መንግሥት ምስል ማቆየቱ አስፈላጊ ነው። አ.ት፡ “በንጉሡ በትረ መንግሥት” ወይም “የንጉሡ በትረ መንግሥት በሚወክለው ሥልጣን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሚመጣው ሰይፍ እንዲህ ያሉትን በትሮች ሁሉ ይጠላል

እዚህ ጋ “ሰይፍ” ሰዎችን ሊያጠቃ እንደሚመጣ በሰውኛ ተገልጿል። ይህ፣ “ሰይፍ” የንጉሡን በትረ መንግሥት የጠላው ይመስል፣ ንጉሡ “ሰይፍ”ን መቋቋም ያለመቻሉን ይናገራል። አ.ት፡ “ሰይፍ እንደ ማንኛውም ገዢ በእርሱ በትረ መንግሥት ላይ የበላይ ይሆናል” ወይም “ንጉሡ ሰይፍ በሚመጣበት ጊዜ መቋቋም አይችልም” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

እንዲህ ያለው በትር

ይህ ሐረግ በንጉሡ በትረ መንግሥት ላይ “በትር” ብሎ ለመሳለቅ ጥቅም ላይ ውላል። አ.ት፡ “እንዲህ ያለው በትረ መንግሥት” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)

ሰይፉ እንዲወለወል ይሰጣል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰይፉን እወለውለዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ከዚያም በእጅ የሚያዝ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም ተገቢነት ያለው ሰው በእጁ ይይዘዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እርሱም በሚገድለው ሰው እጅ ላይ ይሰጣል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ገዳዩ እንዲጠቀምበት ተዘጋጅታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)