am_tn/ezk/21/08.md

1.5 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሰይፍ! ሰይፍ! ተስሏል፣ ተወልውሏልም

ይህ ምንባብ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለማጥቃት የሚጠቀምባቸውን የጠላት ሰራዊት በዘይቤአዊ አነጋገር የእግዚአብሔርን ሰይፍ በማለት ይገልጸል።ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር እዚህ ጋ ይጀምርና እስከ ሕዝቅኤል 21፡17 ድረስ ይቀጥላል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ተስሏል፣ ተወልውሏልም

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ሰይፉ አንድ ሰው እንዲጠቀምበት መዘጋጀቱን ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የተሳለና የተወለወለ ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ተወልውሏል

አንድ ሰው በሻካራ ነገር በመጥረግ ሰይፉ ስለታም፣ አንጸባራቂና ንጹሕ እንዲሆን አድርጎታል።