am_tn/ezk/21/06.md

2.9 KiB

ወገቡ እንደ ተቆረጠ ሰው አቃስት

የመልዕክቱ አጃቢ ምልክት እንዲሆንለት ያቃስት ዘንድ እግዚአብሔር ለሕዝቅኤል ይነግረዋል። ሆዱን በብርቱ የታመመ ያህል በኃይል እንዲያቃስት ይነግረዋል። “ወገብህ በታላቅ ሕመም ላይ እንዳለ ያህል በኃይል አቃስት” ወይም “ከታላቅ ሀዘን ጋር በኃይል አቃስት”(የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በምሬት አቃስት

“ከታላቅ ሀዘን ጋር” ወይም “በመሪር ሀዘን”

በዐይኖቻቸው ፊት

እዚህ ጋ እስራኤላውያን ስላዩት ነገር አጽንዖት ለመስጠት በ”ዐይኖቻቸው” ተወክለዋል። አ.ት፡ “በፊታቸው” ወይም “በእስራኤል ሕዝብ ፊት”

እየመጣ ያለው ወሬ

ይህ በቶሎ ወደ እነርሱ እንደሚመጣ ሰው ተደርጎ የተነገረው ስለ “ወሬ” ነው። አ.ት፡ “በቅርቡ የሚሰሙት ወሬ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)

ልብ ሁሉ ይቀልጣል

ይህ ልባቸው የሚቀልጥ ይመስል ሰዎች እንደሚፈሩ ይናገራል። በተጨማሪም፣ ይህ ከፍርሐት የተነሣ ራሳቸውን እንደሚስቱ ይናገራል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ይፈራል” (Synecdoche እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይደናቀፋል

“ይደክማል”

መንፈስ ሁሉ ይዝላል

ይህ የሚናገረው መንፈሳቸው ይዝል ይመስል ሰዎች በመንፈሳቸው እንደሚፈሩ ይናገራል። አ.ት፡ “ሁሉም በውስጥ ሰውነቱ ይፈራል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጉልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይፈሳል

“ጉልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይደክማል”። ይህ ሰዎች ከብርቱ ፍርሐታቸው የተነሣ ፊኛቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው በራሳቸው ላይ እንደሚሸኑ የሚያመለክት አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እግር ሁሉ በሽንት ይረጥባል” ወይም “እያንዳንዱ ሽንቱን መቆጣጠር ያቅተዋል”

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)