am_tn/ezk/21/01.md

3.1 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ” ወይም “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። ይህንን በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።

ፊትህን በኢየሩሳሌም አቅጣጫ አቅና

ይህ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች እንደሚቀጡ ምልክት ይሆናቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም አቅጣጫ እንዲያፈጥ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም ላይ አፍጥጥ” ወይም “በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ጉዳት እንዲደርስባቸው በኢየሩሳሌም ላይ አፍጥጥ”

ፊትህን በኢየሩሳሌም አቅጣጫ አቅና

ኢየሩሳሌም ርቀት ላይ ነበረች፣ በመሆኑም ሕዝቅኤል ሊያያት አይችልም፣ ነገር ግን በዚያ አቅጣጫ ማፍጠጡ እርሷን የመጉዳት ምልክት ይሆናል። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 6፡2 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ወደ ኢየሩሳሌም ዙርና አፍጥጥ” ወይም “በዚያ ያሉ ሰዎች ጉዳት እንዲደርስባቸው በኢየሩሳሌም አቅጣጫ አፍጥጥ”

ሰይፌን ከሰገባው እመዛለሁ፣ ከአንቺም ጻድቁንና ክፉዉን ሰው እቆርጣለሁ

ይህ፣ እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች በራሱ ሰይፍ የገደላቸው በሚመስልበት መልኩ እንዲሞቱ እንደሚያደርጋቸው ይናገራል። አ.ት፡ “እናንተን ተቃውሜአለሁ፤ ይኸውም፣ በመካከላችሁ ያሉትን ጻድቃኑንና ክፉዎቹን ሰዎች ለመግደል ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝኩ ያህል ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ጻድቁንና ክፉዉን ሰው

“ጻድቅ ሰዎችና ክፉዎች ሰዎች”። ይህ የሚያመለክተው አንድ ጻድቅን እና አንድ ክፉ ሰውን ብቻ ሳይሆን በጣም ብዙ ሰዎችን ነው።

ሰገባ

ማንም በማይጠቀምበት ጊዜ ሰይፉን የሚይዘውና የሚሸፍነው ነገር ነው

ቁረጥ

ይህ የግደል ሻል ያለ ቃል ነው። አ.ት፡ “ግደል”