am_tn/ezk/20/42.md

1.3 KiB

ለመማል እጄን አንሥቻለሁ

እዚህ ጋ “እጄን አንሥቻለሁ” የሚለው አባባል ለማድረግ የማለውን ነገር በእርግጠኝነት እንደሚያደርገው የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “በጽኑ መሐላ ምያለሁ” (See: Symbolic Action)

ትዝ ይላችኋል

የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም ማስታወስ ማለት ነው። አ.ት፡ “ታስታውሳላችሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ራሳችሁን አርክሳችኋል

ለእግዚአብሔር ዓላማ ተቀባይነትን ያላገኘ ያ ሰው እንደ ረከሰ ተቆጥሮ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በዐይኖቻችሁ ፊት ራሳችሁን ትንቃላችሁ

እዚህ ጋ ዐይን ማየትን፣ ማየትም አሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል። አ.ት፡ “ራሳችሁን ትጠላላችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ስለ ስሜ ስል

እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል የሚወክለው የእግዚአብሔርን ዝና ነው። አ.ት፡ “በዝናዬ ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)