am_tn/ezk/20/40.md

2.1 KiB

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ቁርባናችሁን ለመጠየቅ

“ቁርባናችሁን እንድታቀርቡ እናንተን ለመጠየቅ”

የመታሰቢያችሁን የመጀመሪያ ፍሬ

እግዚአብሔር ለእርሱ ከሚሰጡት ሁሉ ላይ እጅግ ስለተመረጡት ነገሮች “የመጀመሪያ ፍሬዎች” እንደ ሆኑ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እጅግ የተመረጠ ስጦታዎቻችሁን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቅዱስ ነገራችሁን

“ለእኔ ለመስጠት የለያችኋቸውን ቁርባኖች”

መልካም መዓዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኋለሁ

እግዚአብሔር ሕዝቡ ራሱ የዕጣን ቁርባን እንደሆኑለት አድርጎ እርሱን ስለሚያመልከው ሕዝቡ ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከሕዝቦች አውጥቼ አመጣችኋለሁ፣ ከየሀገራቱም እሰበስባችኋለሁ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን እግዚአብሔር ሕዝቡን ከበተነበት ሀገር ሁሉ መልሶ እንደሚያመጣቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡34 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። (See: Parallelism)

ከተበተናችሁበት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እናንተን ከበተንኩበት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)