am_tn/ezk/20/39.md

892 B

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንዲሰሙኝ

“እንዲታዘዙኝ” ወይም “እንዲያደምጡኝ”

ቅዱስ ስሜን መስደብ

እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል ራሱን እግዚአብሔርን ይወክላል። አ.ት፡ “እኔን ማዋረድ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)