am_tn/ezk/20/36.md

943 B

በበትሬ ስር እንድታልፉ አደርጋችኋለሁ

ይህ በጎቹን በበትሩ ስር እንዲያልፉ በማድረግ የሚቆጥራቸውንና የሚቆጣጠራቸውን የእረኛ ተግባር ያመለክታል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር ከየሀገሩ የሚሰበስባቸውን ሕዝቦቹን ሁሉም መኖራቸውን ለማረጋገጥ ይቆጥራቸዋል። አ.ት፡ “እረኛ በጎቹን እንደሚቆጥራቸው በጥንቃቄ እቆጥራችኋለሁ” ወይም 2) ከበትሩ ስር በሚያልፉበት ጊዜ ታማኙን ታማኝ ካልሆነው ለመለየት እግዚአብሔር እያንዳንዱን ሰው ይቆጣጠራል። አ.ት፡ “እረኛ በጎቹን እንደሚቆጣጠር በጥንቃቄ እቆጣጠራችኋለሁ” የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)