am_tn/ezk/20/33.md

1.5 KiB

ሕያው እንደ መሆኔ

“ሕያው መሆኔ እርግጥ የመሆኑን ያህል”። እግዚአብሔር ቀጥሎ የሚናገረው የተረጋገጠ እውነት መሆኑን ለማሳየት ይህንን አገላለጽ ይጠቀማል። ይህ ጽኑ ተስፋ የመስጫ መንገድ ነው። አ.ት፡ “ጽኑ መሐላ አደርጋለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋችም ክንድ

“እጅ” እና “ክንድ” የሚሉት ቃላት ሁለቱም የሚወክሉት ኃይልን ነው። አ.ት፡ “በጣም ታላቅ በሆነ ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በእናንተ ላይ የሚፈሰውን ቁጣ

በሕዝቡ ላይ የሚያፈሰው ቁጣው ፈሳሽ የሆነ ነገር ይመስል እግዚአብሔር ቁጣውን ስለ መግለጽ ይናገራል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእናንተ ላይ የማፈሰው ቁጣ” ወይም “በእናንተ ላይ ቁጣዬን እገልጻለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በተበተናችሁባቸው መካከል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እናንተን በበተንኩባቸው መካከል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)