am_tn/ezk/20/25.md

1.6 KiB

ከዚያም እኔ ደግሞ መልካም ያልሆኑትን ሥርዓቶችና ሊኖሩበት ያልቻሉባቸውን ሕግጋት ሰጠዃቸው

በዚህ ሐረግ ውስጥ ያለው ሥርዓቶች የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ሕግ አያመለክትም። መልካም ባልሆኑት በሰዎች ሕጎችና ፍርዶች እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው።

ሰጣቸው

“እነርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር ከግብፅ ያወጣቸውን የእነርሱን ልጆች ያመለክታል።

በስጦታዎቻቸው

እዚህ ጋ “ስጦታዎች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ለሚያመልኳቸው ጣዖታት የሚያቀርቧቸውን መስዋዕት ነው። አ.ት፡ “በመስዋዕቶቻቸው ምክንያት” ወይም “ለጣዖታት ስጦታን ስለ ሰጡ”

የማህፀንን በኩር ሁሉ መስዋዕት አደረጉ

“የማህፀን በኩር” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ከሴት የሚወለደውን የመጀመሪያ ልጅ ነው። “መስዋዕት አደረጉ” የሚለው ሐረግ “መስዋዕት” ከሚለው ግሥ ጋር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የእያንዳንዷን ሴት የመጀመሪያ ልጅ ሰዉ”

በእሳት እንዲያልፉ አደረጓቸው

ለጣዖቶቻቸው የሚቃጠል መስዋዕት ይሆኑ ዘንድ ልጆቻቸውን በእሳት እንዲያልፉ ማድረጋቸው ግልጽ አይደለም። አ.ት፡ “እንደሚቃጠል መስዋዕት አድርገው ሰዉአቸው”