am_tn/ezk/20/23.md

1.1 KiB

እኔ ራሴ ደግሞ ለመማል እጄን እንሥቻለሁ

እዚህ ጋ “እጄን አንሥቻለሁ” የሚለው ሐረግ ለማድረግ የማለውን ቃል ያለ ጥርጥር እንደሚያደርገው የሚያሳይ ምልክታዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “እኔ ራሴ ጽኑ መሐላ ምያለሁ”

በሀገራት መካከል በምበትናቸውና በምድር ሁሉ ላይ በምዘራቸው ጊዜ

የእነዚህ ሁለት ሐረጎች መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 12፡15 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እርስ በእርሳቸው እንዲለያዩና በተለያየ ሀገር እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ”

ዐይኖቻቸው የአባቶቻቸውን ጣዖታት ይናፍቃሉ

እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚለው ቃል የሚወክለው ያመልካቸው ዘንድ ጣዖታትን የሚመለከትን ሰው ነው። አ.ት፡ “የአባቶቻቸውን ጣዖታት ይናፍቁ ነበር”