am_tn/ezk/20/13.md

2.4 KiB

በሥርዓቴ አልሄዱም

ሥርዓቶቹን መታዘዝ አንድ ሰው የሚራመድባቸው መንገዶች የሆኑ ይመስል እግዚአብሔር ሥርዓቶቹን ስለ መታዘዝ ይናገራል። አ.ት፡ “ሥርዓቶቼን አልታዘዙም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ንዴቴን በላያቸው ላይ አፈሳለሁ

ንዴቱ በእነርሱ ላይ የሚያፈሰው ፈሳሽ ይመስል እግዚአብሔር እነርሱን በመቅጣት ንዴቱን እንደሚገልጽ ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡8 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእነርሱ ላይ ንዴቴን አሳያለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነርሱን ለመጨረስ

“ለመጨረስ” የሚለው ቃል እነርሱን መግደልን ያመለክታል። አ.ት፡ “እነርሱን ለመግደል” (See: Euphemism)

ስለ ስሜ ስል አደረግሁ

እዚህ ጋ “ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ዝና ይወክላል። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡9 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ስለ ዝናዬ ስል አደረግሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በሀገሮች ዓይን ፊት እንዳይሰደብ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡9 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በሀገሮች ዓይን ፊት ሰዎች እንዳይሰድቡት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በሀገራቱ ዐይን ፊት

እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚያመለክተው በእነዚያ ቦታዎች የሚኖረውን ሕዝብ ነው። ዐይኖች ማየትን፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላሉ። ይህንን በሕዝቅኤል 20፡9 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በሌሎች ሀገሮች በሚኖሩ ሰዎች አስተሳሰብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከግብፅ ባወጣኋቸው ዐይን ፊት

“ሕዝቤን ከግብፅ አውጥቼ በእነርሱ ፊት ያመጣሁ”