am_tn/ezk/19/12.md

1.1 KiB

የወይኑ ተክል በንዴት ተነቀለና ተጣለ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የወይኑን ተክል በንዴት ነቀለና ጣለው” ወይም “የወይኑን ተክል ሰዎች በንዴት ነቀሉና ጣሉት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ጠንካራ ቅርንጫፎቹ ተሰበሩና ጠወለጉ

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ጠንካራ ቅርንጫፎቹን ሰበራቸውና ጠወለጉ” ወይም “ሰዎች ጠንካራ ቅርንጫፎቹን ሰበሯቸውና ጠወለጉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በድርቅ እና በጥማት ምድር

በጣም የደረቀው ምድር እንደ ተጠማ ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “በጣም በደረቀው የድርቅ ምድር ላይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)