am_tn/ezk/19/10.md

1.2 KiB

በደምሽ ላይ የተተከለ የወይን ተክል

“ደም” ሊወክል የሚችልባቸው ትርጉሞች 1) ሰዎችን የገደሉት የይሁዳ ንገሥታት ሁከት። አ.ት፡ “ሁከትን በመጠቀም የተተከለ የወይን ተክል” ወይም 2) የብልጽግና ምልክት የሆነው የይሁዳ የተትረፈረፈ ወይን። አ.ት፡ “በብልጽግናችሁ የተተከለ የወይን ተክል”

ለበትረ መንግሥትነት ጥቅም ላይ የዋሉ ጠንካራ ቅርንጫፎች

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች በትረ መንግሥት ለመሥራት የተጠቀሙበት ጠንካራ ቅርንጫፍ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ርዝመቱ በቅጠላ ቅጠሉ ታላቅነት ይታይ ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቅጠላ ቅጠሎቹ ታላቅነት ሰዎች ምን ያህል ረጅም እንደነበረ ማየት ይችሉ ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)