am_tn/ezk/18/31.md

1.9 KiB

ያደረጋችሁትን መተላለፍ ሁሉ ከራሳችሁ ላይ ጣሉት

መተላለፍ እንደ ልብስ አውልቀው የሚጥሉት ቁስ ይመስል ሕዝቡ የሚያደርገውን መተላለፍ ለማቆም እንዲወስን እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ካደረጋችሁት መተላለፍ ሁሉ ራቁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ለራሳችሁ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ አድርጉ

እዚህ ጋ “ልብ” የሚለው ቃል የሚወክለው ፈቃድንና ስሜትን ሲሆን “መንፈስ” የሚለው ቃል ደግሞ አሳብንና ጸባይን ይወክላል። አ.ት፡ “ለራሳችሁ አዲስ ስሜትና አዲስ አስተሳሰብ ይኑራችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?

እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለማጽናናት ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የምትሞቱበት ምንም ምክንያት የለም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)