am_tn/ezk/18/29.md

2.4 KiB

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የጌታ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም . . . መንገዴ ፍትሐዊ ያልሆነው እንዴት ነው . . . ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ ነው

ድርጊቶች ወይም ጸባዮች ሰው እንደሚጓዝባቸው መንገዶች ተደርገው ተነግረዋል። አ.ት፡ “ጌታ በፍትሐዊነት አያደርግም . . . በፍትሐዊነት የማላደርገው እንዴት ነው . . . በፍትሐዊነት የማታደርጉ እናንተ ናችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እንደ መንገዶቹ

እግዚአብሔር በመንገድ ላይ እንደሚሄድ ሰው አድርጎ የሚናገረው ስለ ሰው ሥራ ነው። አ.ት፡ “እንደ ሥራው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የኃጢአት ማሰናከያ እንዳይሆኑባችሁ ከመተላለፋችሁ ሁሉ ተመለሱ

ሰዎች የሚሰናከሉበት ማሰናከያ የሆነ ይመስል እግዚአብሔር ሰዎች በእርሱ ላይ እንዲያምጹ ስለሚያደርጋቸው “መተላለፍ” ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የኃጢአት ማሰናከያ እንዳይሆኑባችሁ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ማሰናከያ ሰውዬው የበለጠ ኃጢአት እንዲሠራ ምክንያት ይሆነዋል። አ.ት፡ “የበለጠ ኃጢአት እንድትሠሩ ምክንያት የሚሆንባችሁን ማሰናከያ” ወይም 2) “ኃጢአት” የሚለው ቃል አንድ ሰው ስለ ኃጢአቱ ለሚቀበለው ቅጣት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ወደ ቅጣታችሁ የሚመራችሁን ማሰናከያ” የሚሉት ናቸው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)