am_tn/ezk/18/25.md

1.6 KiB

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መንገዶቼ ፍትሐዊ አይደሉም?

አሉታዊው መልስ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “መንገዶቼ ፍትሐዊ ናቸው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?

አዎንታዊው መልስ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “ፍትሐዊ ያለሆነው የእናንተ መንገድ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

በእነርሱ ምክንያት ይሞታል . . . ባደረገው ኃጢአት ይሞታል

እነዚህ ሐረጎች የሚደጋግሙት በኃጢአቱ ምክንያት የሞተውን ሰው አሳብ ነው፤ ይኸውም፣ ሞቱ የእርሱ እንጂ የሌላ የማንም ስሕተት አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።