am_tn/ezk/18/24.md

1.0 KiB

ከዚያ በሕይወት ይኖራል?

አሉታዊው መልስ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “ከዚያም በእርግጥ በሕይወት አይኖርም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እርሱ ያደረገው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብም

“መታሰብ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉሙ ማስታወስ ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ያደረገውን ጽድቅ ሁሉ አላስታውስም” (የአነጋገር ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ክህደት

ታማኝ ተደርጎ በተቆጠረ ሰው አማካይነት በሀገር ወይም በእግዚአብሔር ላይ የተፈጸመ ወንጀል

እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል

“እርሱ በኃጢአቱ ምክንያት ይሞታል”