am_tn/ezk/18/23.md

1.7 KiB

እኔ ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአተኛው ሞት እጅግ ደስ ይለኛልን?

እግዚአብሔር ተቃራኒው ላይ አጽንዖት ለመስጠት ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “በኃጢአተኛው ሞት እጅግ ደስ አይለኝም. . . ነገር ግን እጅግ ደስ የሚለኝ በሕይወት ይኖር ዘንድ ከመንገዱ ከተመለሰ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ከመንገዱ በመመለሱ አይደለም

ሰውዬው የሚሄድበት መንገድ በሚመስልበት መልኩ እግዚአብሔር የሚናገረው ስለ ሰው የአኗኗር ዘይቤና ጸባይ ነው። ከአንድ ነገር “መመለስ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉሙ ያንን ነገር ማድረግ ማቆም ማለት ነው። አ.ት፡ “ይኖርበት የነበረውን መንገድ በመተዉ አይደለም” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)