am_tn/ezk/18/19.md

1.3 KiB

የአባቱን ኃጢአት ልጁ የማይሸከመው ለምንድነው?

ኃጢአት ሰውዬው የሚሸከመው ቁስ በሚመስልበት መልኩ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአቱ ኃላፊ ወይም በደለኛ ስለሚሆን ሰው ይናገራል። አ.ት፡ “ልጁ ስለ አባቱ ኃጢአት ኃላፊ የማይሆነው ለምንድነው?” ወይም “ልጁ ስለ አባቱ ኃጢአት በደለኛ የማይሆነው ለምንድነው?” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በትክክል የሚያደርግ ጽድቁ በራሱ ላይ ይሆናል

ጽድቅ በአንድ ሰው ላይ የመሆኑ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም ሰውዬው ስለዚያ ጽድቅ ኃላፊ ነው ማለት ነው። አ.ት፡ “በትክክል የሚያደርግ ለራሱ ጽድቅ ኃላፊ ይሆናል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የኃጢአተኛው ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል

ኃጢአት በሰው ራስ ላይ ይሆናል የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም ሰውዬው ስለዚያ ኃጢአት ኃላፊ ነው ማለት ነው። አ.ት፡ “ኃጢአተኛው ሰው ስለ ራሱ ኃጢአት ኃላፊ ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)