am_tn/ezk/18/14.md

1.8 KiB

እነሆ!

እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አጽንዖት ይሰጣል።

ያ ልጅ በተራሮች ላይ አይበላም

ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በተራሮች ላይ የአሕዛብን አማልክት ያመልኩና መሥዋዕትም ያቀርቡላቸው ነበር። እንዲህ ያለው ሰው እነዚህን በመሳሰሉ የአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ እንዳልተሳተፈ ያመለክታል። በሕዝቅኤል 18 ፡6 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ያ ልጅ በተራሮች ላይ ለጣዖታት የተሰዋውን ሥጋ አይበላም”

ዓይኖቹን ወደ ጣዖታት አያነሣም

“ዓይኖቹን ማንሣት” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ወደ አንድ ነገር መመልከትን ያመለክታል። ወደ ጣዖታት የማመላከቱ አኳኋን የሚወክለው ጣዖታትን ማምለክን ወይም ወደ እነርሱ መጸለይን ነው። በሕዝቅኤል 18፡6 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጣዖታትን አያመልክም” ወይም “ወደ ጣዖታት አይጸልይም”

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)