am_tn/ezk/18/10.md

1002 B

ደምን የሚያፈስ

ይህ ሐረግ በየትኛውም መልክ የሚፈጸም ግድያን ይወክላል። አ.ት፡ “የሚገድል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእነዚህ ነገሮች የትኛውንም

ይህ እግዚአብሔር በሕዝቅኤል 18፡5 መጀመሪያ ላይ የጠቀሰውን ኃጢአታዊ ተግባር ያመለክታል።

በተራሮች ላይ ይበላል

ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በተራሮች ላይ የአሕዛብን አማልክት ያመልኩና መሥዋዕትም ያቀርቡላቸው ነበር። እንዲህ ያለው ሰው እነዚህን በመሳሰሉ የአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ እንደተሳተፈ ያመለክታል። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 18፡5 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በተራሮቹ ላይ ለጣዖታት የተሰዋውን ሥጋ ይበላል”