am_tn/ezk/18/05.md

1.6 KiB

በተራሮች ላይ አይበላም

ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በተራሮች ላይ የአሕዛብን አማልክት ያመልኩና መሥዋዕትም ያቀርቡላቸው ነበር። እንዲህ ያለው ሰው እነዚህን በመሳሰሉ የአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ እንዳልተሳተፈ ያመለክታል።

ዓይኖቹን ወደ ጣዖታት አያነሣም

“ዓይኖችን ማንሣት” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ወደ አንድ ነገር መመልከትን ያመለክታል። ወደ ጣዖታት የማመልከቱ አኳኋን የሚወክለው ጣዖታትን ማምለክን ወይም ወደ እነርሱ መጸለይን ነው። አ.ት፡ “ጣዖታትን ማምለክ” ወይም “ወደ ጣዖታት መጸለይ”

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በወር አበባዋ ወቅት ወደ ሴት ቀርቧል

ከእርሷ ጋር ለመተኛት ወደ ሴቲቱ አለመቅረቡ ግልጽ አይደለም። አ.ት፡ “በወር አበባዋ ወቅት ከእርሷ ጋር ለመተኛት ወደ ሴት ቀርቧል”