am_tn/ezk/18/01.md

2.2 KiB

የእግዚአብሔር ቃል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል መጣ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ ስለ አንድ ነገር የነገራቸውን ለማሳወቅ ጥቅም ላይ የዋለ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንደገና እግዚአብሔር ተናገረኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

‘አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፣ የልጆችም ጥርስ ደነዘ’. . . ይህንን ምሳሌ የምትጠቀሙ ምን ማለታችሁ ነው?

ሕዝቅኤል አስቀድሞ ስለሚያውቀው አንድ ነገር ለማስታወስ እግዚአብሔር ይህንን ምላሽ የማይሻ ጥያቄ ይጠይቃል። ጥያቄው ምሳሌውን ለሚጠቀሙ ሰዎች ተግሳጽ ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል ምድር የሚኖሩ ሰዎች ይህ ምሳሌ አላቸው፣ . . . ‘አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፣ የልጆችም ጥርስ ደነዘ’”።(ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ይህንን ምሳሌ የምትጠቀሙ ምን ማለታችሁ ነው?

እዚህ ጋ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው።

የእስራኤል ምድር

ይህ የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፣ የልጆችም ጥርስ ደነዘ

የዚህ ምሳሌ ትርጉም ልጆች የሚለማመዱት የአባቶቻቸውን የሥራ ውጤ ነው የሚል ነው። (ምሳሌዎች የሚለውን ተመልከት)

የልጆችም ጥርስ ደነዘ

“ጥርሶች ደነዙ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ አንድ ሰው ያልበሰለውን ወይም የሚጎመዝዘውን ፍሬ ሲበላ አፉ ላይ የሚሰማውን የመጎምዘዝ ስሜት ያመለክታል። አ.ት፡ “ልጆች አፋቸው ውስጥ ጎምዛዛ ጣዕም ተሰማቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)