am_tn/ezk/17/15.md

2.5 KiB

ይሳካለት ይሆን?

አሉታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በእርግጠኝነት አይሳካለትም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ እርሱ ያመልጥ ይሆን?

አሉታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ እርሱ አያመልጥም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ቃል ኪዳኑን ቢያፈርስ፣ እርሱ ያመልጣል?

አሉታዊው ምላሽ ላይ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር ይህንን ዋነኛ ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ቃል ኪዳኑን ቢያፈርስ ፈጽሞ አያመልጥም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ሕያው እንደ መሆኔ

“ሕያው መሆኔ እርግጥ የመሆኑን ያህል”። እግዚአብሔር ቀጥሎ የሚናገረው የተረጋገጠ እውነት መሆኑን ለማሳየት ይህንን አገላለጽ ይጠቀማል። ይህ ጽኑ ተስፋ የመስጫ መንገድ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጽኑ መሐላ አደርጋለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

እርሱን ያነገሠችው የንጉሡ ምድር፣ መሐላውን ያቃለለ ንጉሥ

“እርሱን በይሁዳ ላይ ያነገሠው የባቢሎን ንጉሥ ምድር፣ መሐላውን ያቃለለው የባቢሎን ንጉሥ”