am_tn/ezk/17/05.md

1.7 KiB

ደግሞም እርሱ ወሰደ

“እርሱ” የሚለው ቃል በምሳሌው ውስጥ ንስሩ ነው።

ለም ዐፈር

“ጥሩ መሬት”

ብዙ ውሃ ባለበት አጠገብ አኖረው

“ንስሩ ዘሩን ብዙ ውሃ ባለበት ቦታ ላይ ተከለው”

እንደ ውሃ ዳር ዛፍ . . . ተከለው

የውሃ ዳር ዛፍ የሚበቅለው ብዙ ውሃ ባለበት ስፍራ ነው። ንስሩ ዘሩን እንደ ውሃ ዳር ዛፍ ከተከለው ይህ ማለት ብዙ ውሃ ባለበት ቦታ ላይ ተክሎታል ማለት ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው የውሃ ዳርን ዛፍ በውሃ አጠገብ እንደሚተክል ዘሩን ተክሎታል”

ከዚያም አጎነቆለ

“ከዚያም ዘሩ ወደ ተክልነት ማደግ ጀመረ”

የወይኑ ሐረግ በምድር ላይ ተዘረጋ

“በምድር ላይ የሚስፋፋ የወይን ሐረግ”

ቅርንጫፎቹ ወደ እርሱ ተመለሱ

የወይኑ ቅርንጫፎች ወደ ንስሩ አቅጣጫ ተመለሱ። ይህ ማለት ወደ ላይ ወደ ሰማይ ማደግ ጀመሩ።

ሥሮቹ ከበታቹ አደጉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ሥሮቹ ከበታቹ ወዳለው መሬት ውስጥ አደጉ” ወይም “የወይን ሐረጉ ሥሮች ከንስሩ በታች አደጉ”።

ከዚያም የወይን ተክል ሆነ

“የወይን ተክል የሚያድገው እንደዚህ ነው”

ቅርንጫፎችን አወጣ፣ ለምለም ቅጠሎችንም አስረዘመ

“ቅርንጫፎች አሳደገ፣ ለምለም ቅጠሎቹንም አስፋፋ”