am_tn/ezk/17/01.md

2.5 KiB

የእግዚአብሔር ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢያቱ ወይም ለሕዝቡ አንድን ነገር ለማስታወቅ የሚጠቀምበት የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይህንን መልዕክት ተናገረ” ወይም “እነዚህን ቃላት እግዚአብሔር ተናገረ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ

“የሰብዓዊ ፍጡር ልጅ” ወይም “ከሰው የተወለደ ልጅ”። ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን አፅንኦት ለመስጠት እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ በማለት ይጠራዋል። እግዚአብሔር ዘላለማዊና ኃያል ነው፣ ሰዎች ግን አይደሉም። አ.ት፡ “ሟች ሰው” ወይም “ሰው”

ዕንቆቅልሽ አቅርብላቸው፣ በምሳሌም ተናገር

“ስለ እርሱ እንዲያስቡ ዕንቆቅልሽን ስጣቸው” ወይም “ይህንን ታሪክ እንደ ማብራሪያ ንገራቸው”

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ቤተሰቦች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፤ በመሆኑም፣ ይህ ከረጅም ዓመታት ጀምሮ ያሉትን የያዕቆብን ዘሮች፣ እስራኤላውያንን ያመለክታል። ይህንን በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በላባ የተሞሉ ረጃጅም ክንፎች

“የክንፎቹ ጫፎች ረጃጅምና በላባ የተሞሉ ነበሩ”። “ክንፍ” የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ ትርጉሙ የክንፎቹን ውጫዊ ጫፍ ማለት ነው።

ዥንጉርጉር ነበር

የንስሩ ላባዎች ብዙ የተለያዩ ቀለማት ነበሩት።

እርሱ የቅርንጫፉን ቀንበጥ ሰበረ

“እርሱ የዛፉን የላይኛውን ጫፍ ሰበረ”

ወሰዳቸው

“የዛፉን ጫፍ ወሰደ” ወይም “ጫፎቹን ወሰዳቸው”

እርሱን በነጋዴዎች ከተማ ተከለው

“እርሱን ብዙ ነጋዴዎች በነበሩባት ከተማ ተከለው”። ነጋዴ ሸቀጦችን የሚሸጥ ሰው ነው።