am_tn/ezk/16/56.md

2.0 KiB

እህትሽ ሰዶም እንኳን በአፍሽ አልተጠራችም

እዚህ ጋ “አፍ” የሚለው ቃል የሚወክለው ተናጋሪውን ሰው ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የእህትሽን የሰዶምን ስም እንኳን አልጠራሽም” (Synecdoche እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ኃጢአተኝነትሽ ከመገለጡ በፊት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ኃጢአተኝነትሽን ከመግለጥሽ በፊት” ወይም “ኃጢአተኝነትሽን ከመግለጤ በፊት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

አንቺ መሣለቂያ ነሽ

ይህ ሰዎች ስለ አንዳች ነገር በመጥፎ የሚናገሩላትን ኢየሩሳሌምን ያመለክታል።

ለኤዶም ሴቶች ልጆችና ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች በሙሉ

እዚህ ጋ የኤዶምና የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች የሆኑ ይመስል እግዚአብሔር የሚናገረው ስለ ኤዶምና ፍልስጥኤም ነው። ከተሞቹ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላሉ። አ.ት፡ “ኤዶማውያን እና የፍልስጥኤም ሰዎች በሙሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

መናቅ

በጣም መጥላት

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)