am_tn/ezk/16/35.md

1.4 KiB

ዝሙትሽን አፈሰስሽ

ፈሳሽ የሆነ ይመስል እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ዝሙት ይናገራል፤ ይህንን ብርቱ የዝሙት ፍላጎትዋን ለማርካት ደጋግማ መፈጸሟን ደግሞ ከዕቃ መያዣው እንደሚፈስ ፈሳሽ አድርጎ ይገልጸዋል። አ.ት፡ “የዝሙት ፍላጎትሽን ለማርካት በተደጋጋሚ ፈጸምሽው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዝሙትሽን አፈሰስሽ

አንዳንድ የቅርብ ዓመታት ትርጉሞች “ብልጽግናሽን አፈሰስሽ” ብለው ይተረጉሙታል።

የልጆችሽን ደም ሰጠሻቸው

ይህ የሚያመለክተው ለጣዖታት መስዋዕት እንዲሆኑ የተገደሉትን ልጆች ነው።

እነሆ

እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል።

ስለዚህ ሙሉ ራቁትነትሽን ያያሉ

በሌሎች ፊት የአንድን ሰው ልብስ መግፈፍ ያንን ሰው ለማዋረድ በማሰብ የሚደረግ ተግባር ነው። “ራቁትነት” የሚለው ቃል እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ራቁትሽን መሆንሽን ማየት ይችላሉ”