am_tn/ezk/16/30.md

1.8 KiB

እነዚህን ሁሉ ነገሮች፣ እፍረት ዐልባ የአመንዝራነት ሥራ የምትሠሪው . . . ልብሽ ምን ያህል ታማሚ ቢሆን ነው?

እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለመገሰጽ ምላሽ የማይሻውን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህን ሁሉ ነገሮች፣ እፍረት ዐልባ የአመንዝራነት ተግባር የምትፈጽሚው ልብሽ በጣም ስለ ታመመ መሆን አለበት!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ልብሽ ምን ያህል ታማሚ ቢሆን ነው

እዚህ ጋ “ልብ” የሚለው ቃል ፈቃድን እና ስሜትን ይወክላል። ልቧ የታመመ ይመስል ፍላጎቷን ለመቆጣጠር እንዳልቻለች እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ፈቃድሽ ምን ያህል ደካማ የሆነ ሰው ነሽ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በየጎዳናው ራስ ላይ

እግዚአብሔር የጎዳናን መጀመሪያ ራስ እንደ ሆነ አድርጎ ይናገራል። ተመሳሳዩን ሐረግ በሕዝቅኤል 16፡25 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በየጎዳናው መጀመሪያ ላይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የማምለኪያ አዳራሾችሽን ሠራሽ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) ጣዖታቷን የምታመልክበት ወይም 2) የዝሙት ተግባሯን የምትፈጽምበት ሥፍራ ሠርታለች የሚሉት ናቸው። ይህንን በሕዝቅኤል 16፡24 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።