am_tn/ezk/16/27.md

1.3 KiB

ተመልከት!

እዚህ ጋ “ተመልከት” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል።

በእጄ እመታሻለሁ

እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “እንቺን ለመምታት ኃይሌን እጠቀማለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ምግብሽን እቆርጣለሁ

እግዚአብሔር የምግብ አቅርቦት ማቋረጥን ምግብን እንደ መቁረጥ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “የምግብ አቅርቦትሽን አቆማለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሕይወትሽን አሳልፌ እሰጣለሁ

እዚህ ጋ “ሕይወት” ሰውን ይወክላል። አ.ት፡ “አሳልፌ እሰጥሻለሁ”

ለፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች

እዚህ ጋ የፍልስጥኤምን ከተሞች እግዚአብሔር እንደ ፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች አድርጎ ይናገራል። ከተሞቹ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላሉ። አ.ት፡ “የፍልስጥኤም ሰዎች” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)