am_tn/ezk/16/08.md

927 B

ተመልከት!

እዚህ ጋ “ተመልከት” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚመጣው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል።

የፍቅር ጊዜ መጣልሽ

ይህ አባባል ወጣቷ ሴት ለጋብቻ ዕድሜ መድረሷን እግዚአብሔር ዓይቷል ለማለት ነው።

ይህ የጌታ እግዚአብሔር ቃል ነው

እግዚአብሔር የንግግሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ የራሱን ስም በመጥራት ይናገራል። ይህንን በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “እኔ፣ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርኩት ይህንን ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)