am_tn/ezk/16/04.md

836 B

እናትሽ እንብርትሽን አልቆረጠችውም

እዚህ ጋ “እንብርት” የሚያመለክተው ከእንብርት ጋር የተያያዘውን እትብት ያመለክታል። አ.ት፡ “እናትሽ እትብትሽን አልቆረጠችውም”

የማንም ዐይን አልራራልሽም

እዚህ ጋ “ዐይን” የሚለው ቃል የሚወክለው የሚያየውን ሰው ነው። አ.ት፡ “ካየሽ ሁሉ የራራልሽ የለም”

ሕይወትሽ የተጠላ

“ወላጆችሽ ጠልተውሽ ስለ ነበር”

ሜዳ ላይ ተጥለሽ ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወላጆችሽ ሜዳ ላይ ጥለውሽ ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)